Ethiopia

የሃይማኖት ሽፋን ግጭት

በሃይማኖት ሽፋን በህዝቦች መካከል ግጭት ለማስነሳት የሚሞክሩ ግለሰቦችን ማውገዝ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ “ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/