InternationalNews

የኤሊኒኖ  መከሰትና ጥንቃቄ

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት አዲስ የኤሊኒኖ መከሰቱትን አረጋገጠ፡፡

ድርጅትቱ ባወጣው መግለጫ፣ አዲስ የኤሊኖ ክስተት እንደሚፈጠር ገልፆ  ክስተቱ ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2026 ባሉት ወራት ውስጥ የማጋጠም ዕድሉ 80 በመቶ መሆኑን ነው የተናገረው፡፡

የፓስፊክ ውቅያኖስ የውስጠኛው ክፍል ውሃ ከተለመደው በላይ ሙቀቱ መጨመሩ ለዚህ አዲስ የኤሊኖ መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ሆኗልም ተብሏል።

ይህ አዲስ የኤሊኒኖ ክስተት በኢትዮጵያ ዋነኛ የምግብ ምርት ወቅት በሆነው ከሰኔ እስከ መስከረም የክረምት ዝናብ ላይ ከመደበኛ በታች ማለትም ዝቅተኛ ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል የሚል ትንበያም ነው የተቀመጠው፡፡

ከዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከመደበኛው በላይ የሆነ ከፍተኛ ሙቀት የሚያስከትል መሆኑንና ይህም የአፈር እርጥበትን በማድረቅ በሰብልና በከብቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ተሰግቷል።

በተቃራኒው፣ ኤሊኒኖን እየበረታ ሲሄድ ከዓመቱ ማጠናቀቂያ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ ባሉት ወራት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ቆላማ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ እና የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል።

ሀገራት ይህንን አዲስ የኤሊኒኖ መከሰት እንደ አስቸኳይ የአየር ንብረት ማስጠንቀቂያ ወስደው የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv