EthiopiaNews

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ464 ሚሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ።

የገንዘብ ድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ያፀደቀውን የ464 ሚሊየን ዶላር ብድር ይፋ ያደረገው የአምስተኛው ዙር የተራዘመ ብድር አቅርቦት መጠናቀቁን አስመልክቶ ትናንት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ ነው።

የገንዘብ ድርጅቱ ካፀደቀው ጠቅላላ ብድሩ ውስጥ 200 ሚሊየን ዶላር ያክሉ የኢራን ጦርነት በነዳጅ የአቅርቦት ላይ ያደረሰውን ጫና ኢትዮጵያ እንድትቋቋም በሚል የተመደበ ነው።

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ እንድታገኝ የፀደቀላትን የ464 ሚሊየን ዶላር ጨምሮ አጠቃላይ ከገንዘብ ድርጅቱ ያገኘችው ገንዘብ 2.6 ቢሊየን ዶላር ድርሷል ተብሏል።መረጃው ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews