የዜሌንስኪ ደብዳቤ ለፑቲን
ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ለሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት እንነጋገር የሚል ግልፅ ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰምቷል።
ዜሌንስኪ በደብዳቤያቸው የአውሮፓ ጦርነት የአሜሪካን ቀልብ በድጋሚ እስኪስብ መጠበቅ የለብንም ያሉ ሲሆን የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ሁለቱ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው መምከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
ዜሌንስኪ አክለውም ሁለቱ መሪዎች ጦርነቱን በሰላማዊ መንገድ ለማስቆም በሚነጋገሩበት ወቅት ሙሉ ለሙሉ የተኩስ አቁም መደረግ እንዳለበት አመልክተዋል፡፡
የክሬምሊን ባለስልጣናት የዜሌንስኪ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ጠቁሞው ዜሌንስኪ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መነጋገር ከፈለጉ ሞስኮ መምጣት እንደሚችሉ ቢገልጹም ዜሌንስኪ ግን ፑቲንን በቱርክ ወይም በስዊዘርላንድ ማግኘት እንደሚሹ ነው የጠቆሙት፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ስለዜሌንስኪ ደብዳቤ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ሁለቱ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው ቢመክሩ መልካም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
