EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብርን ትናንት በይፋ አስጀመሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብርን ትናንት በይፋ አስጀመሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመው ዘንድሮም ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኝ በመትከል በአጠቃላይ 56 ቢሊየን እንደሚደርስ በመርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ኮፕ-32ን ስታስተናግድ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች ሀገር ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎች ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጭው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews