EthiopiaNews

ፕሬዚዳንት ማክሮን በአዲስ አበባ

🔸ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር መወያየታቸውን ተናገሩ።

🔸ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
‎
🔸‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ቁልፍ ስምምነቶች ልውውጥን በጋራ መምራታቸውን ገልጸዋል።

🔸በዚሁም የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት እና የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ ይገኙበታል ነው ያሉት።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews