EthiopiaNews

የመራጮች ምዝገባ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ እንደቀሩት አስታወቀ።

ቦርዱ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በዲጅታል እና በማኑዋል አማራጭ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

ቦርዱ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ46 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን ገልጿል።

ለመራጭነት ከተመዘገቡት ዜጎች ውስጥ 21 ሚሊየን 515 ሺህ 693 ሴቶች ሲሆኑ፤ 25 ሚሊየን 217 ሺህ 202 ደግሞ ወንዶች ናቸው።

መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv