EthiopiaNews

የምክክር ጉባኤው ሂደት

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ጉባኤው በኮሚሽኑ የአሠራር ሥነ ዘዴ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን የአራት ቀናት ውሎ አስመልክቶ  ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በተያዘለት ዕቅድ እና የአሠራር ሥነ ዘዴ መሠረት እየተከናወነ መኾኑን አስታውቀዋል።

በዚህ ሰሞን ተመካካሪዎች በምክክሩ ወቅት የሚከተሉትን የሥነምግባር ደንብ እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥን በተመለከተ በስምንት ቡድን ተከፍለው ገለጻ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ከኹሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተሳታፊዎችን ማካተቱን ገልጸው፤ በምክክር ጉባኤው የሚደፈቅ ሀሳብ እና የሚተው ድምጽ እንዳይኖር የአሠራር ሥነ ዘዴው በሚፈቅደው መልኩ እንደሚሠራም ተናግረዋል።

በእስካሁኑ ሂደት ያጋጠሙ መጠነኛ የሎጀስቲክስ እና የአተገባበር ክፍተቶችን ኮሚሽኑ እንደሚገነዘብ በመግለጽ፤ ኮሚሽነሮችና የኮሚሽኑ ባለሞያዎች ለተፈጠሩ ክፍተቶች ምላሽ እየሰጡ መኾኑን ኮሚሸነሩ አብራርተዋል።

የምክክር ጉባኤው ስኬታማ እንዲኾን መገናኛ ብዙኃን ለማኅበረሰቡ መረጃ መስጠታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም  ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው።