የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይሄን ያስታወቀው የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው።
ቢሮው ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።
ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል ተብሏል።
ቢሮው ይህ አሰራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፆ ተከራዮች ደግሞ ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከስነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል ብሏል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የተገኘ ነው።
