የሃገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ይሄን ያሉት ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎች ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ፕ/ር መሥፍን አርአያ በሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ለመታደም የመጡ ተመካካሪዎችን በመቀበሌ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ተመካካሪዎች በዚህ ጉባኤ ላይ የመጡት ለመሳተፍ የወከሉትን ማህበረሰብ ድምፅና ምኞት ለማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የጋራ ዕድልና የወደፊት ዕጣ ፈንታ መሠረት ለመጣል ጭምር በመሆኑ ትከሻቸው ላይ የወደቀው ኃላፊነት እጅግ ታላቅና ጥልቅ ነው ብለዋል።
ፕ/ር መሥፍን አርአያ ተመካካሪዎች በምክክራቸው የሚደርሱባቸው ውሳኔዎች፣ የሚፈጥሩት መግባባት እንዲሁም የሚያጸኑት ስምምነት ከዚህ የታሪክ ወቅት ባለፈ ዘልቆ የሚቀጥልና ለሰላማዊት፣ ለዴሞክራሲያዊትና ለተግባባች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ተመካካሪዎች ምክክራቸው በጥበብ፣ በጋራ መከባበርና ለሕዝብ ጥቅም ባላቸው ጽኑ ቁርጠኝነት እንዲመራ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ብሩህ ነገን የሚያሰናዳ እንዲሆን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
መረጃው ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው።
