EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለሀገር የሚተርፍ አሻራ ለማሳረፍ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያን ማጽናት የሚቻለው ሁሉንም ድምፆች እኩል በማድመጥ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም በቁጥር ሰፊ የሆኑት ሕዝቦች የሌሎችን ወገኖች ጥያቄዎች ማድመጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስፋቱና በወሰደው ጊዜ እንዲሁም በሚያስገኘው ውጤት የተለየና ለአፍሪካ ጭምር ተምሳሌት መሆን የሚችል መድረክ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡

ሀገራዊ ምክክር የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተሰብስበው ከሚወስኑት ይልቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመከሩበት ታላቅ መድረክ ነውም ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀገራዊ ምክክሩ በዘመናቸው ታሪክን ፅፈው ማለፍ ለሚፈልጉ እንዲሁም እንደ ሀገር ካሉብን ችግሮቻችን ለመውጣት ትልቅ ዕድል መሆኑንም አንስተዋል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይም ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡