EthiopiaNews

ዋና ኮሚሽነሩ ይሄን ያሉት ዛሬ በተጀመረው የሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ነው።

ዋና ኮሚሽነሩ ምክክሩ የኢትዮጵያን ታላቅነት ለማስቀጠል እንቅፋት የሚኾኑ ጉዳዮችን ለመፍታትም ያገለግላል ብለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ጉባኤው የሀገራችንን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ የጉዞ አቅጣጫ የሚያቀና፣ ለቀጣዩ ትውልድም ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል አዲስ ምእራፍ ከፋች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በምክክር ጉባኤው መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ፣ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።