የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአጨቃጫቂዋ ኩሪል ደሴት ያደረጉት ጉብኝት ከጃፓን ጠንካራ ተቃውሞ ገጠመው።
የሩሲያው መሪ ከአራቱ የኩሪል ደሴቶች ኢቱርፕ የተባለችው ደሴት መጐብኘታቸው በሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ከተገለፀ በኋላ ነው ጃፓን ተቃውሞዋን ያሰማችው።
የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቪሙትሱ ሞቲጊ እንደሚሉት ደሴቷ በታሪክና በዓለምአቀፍ ሕግ መሰረት የጃፓን ይዞታ በመሆኗ አገራቸው የፑቲንን ጉብኝት አጥብቃ ትቃወማለች።
ሞስኮና ቶኪዮ በኩሪል ደሴት ለአስርት ዓመታት በይገባኛል ሲጨቃጨቁ የኖሩ ሲሆን በዚህ ሳቢያም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላም የሰላም ስምምነት አልተፈራረሙም።
