የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጐ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ከምንጊዜውም ወረርሽኞች የከፋ ሊሆን ይችላል እያለ ነው።
የድርጅቱ ኃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም እንደሚሉት አሁን የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ በዚሁ ከቀጠለ በፈረንጆቹ ከ2014 እስከ 2016 የነበረውንና ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች የሞቱበትን ክስተት ሊበልጥ ይችላል።
ባለፈው ግንቦት የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ እስካሁን 4 ሺህ 300 ሰዎች ላይ የታየ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸው አልፏል።
የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣይ ሦስት ወራት የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ማቀዱን ጠቅሶ ይህ ማለት ግን በሽታው ይጠፋል ማለት አይደለም ብሏል።
የአሁኑ ዙር ወረርሽኝ ባለፈው ግንቦት ቢታወቅም በሽታው ግን ከዚያ በፊት በሦስት ወራት ዕድሜ መቀስቀሱን የጤና ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርገዋል።
