EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ8 የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲመካከሩ የቆዩት የአጀንዳ ቡድኖች መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታወቀ።

በሀገር ግንባታ ፣በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብት ፣ እንዲሁም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተመካካሪዎች ስምምነት እንደደረሱ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

ከሁለት ቀናት በፊት በሰላም ግንባታ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በመንግስት አደረጃጀት እና በፖለቲካ ስርዓት ሲመካከሩ የነበሩ ቡድኖች መግባባት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡መረጃው ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው።