EthiopiaNews

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ ዋራ ቀበሌ ልዩ ቦታ ጋላማ በተባለ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ከሀዋሳ ወደ አለታ ወንዶ በመጓዝ ላይ የነበረ ሲኖትራክ መኪና ቆመው በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት በማድረስ እና በኋላም በአንድ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፍን ላይ በመውደቁ አደጋው መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

በዚሁ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቋል።

ነሀሴ 9 ቀን 2018 አ.ም በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ ዋራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጋላማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው በዚሁ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በ11 ተሽከርካሪዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ መሆኑን ገልጾ አሽከርካሪዎች ወቅቱ ዝናባማ በመሆኑ በምሽትም ሆነ በቀን በሚያደርጉት ጉዞ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል::