ፋይዳ ቨርስ በኢትዮጵያ የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ50 ሚሊየን ማለፉን አስታውቋል።
የፋይዳ ቨርስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮዳሄ አርአያስላሴ ይሄን ያሉት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ነው።
ዋና ስራ አስፈፃሚው 14 ሚሊየን የታተመ የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ መሰራጨቱን ተናግረዋል።
ኃላፊው በአሁኑ ሰአት 150 ተቋማት ከፋይዳ ጋር ትስስር መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 12ሺ የፋይዳ መመዝገቢያ ጣቢያዎች መመስረታቸው ተገልጿል።
