ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ይከሰታል የተባለው የኤል-ኒኖ ተፅእኖ በአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እስከ 20 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የኢኮኖሚ ጉዳት የማስከተል እድሉ ሰፊ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው በአፍሪካ የውሃ ሀብትና አጠቃቀም ዙሪያ የሚመክረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሲሆን በጉባኤው ከ20 በላይ ሀገሮች ከ300 በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውም ተነግሯል።
እንዲሁም አፍሪካ ከውሃ ጋር በተገናኘ እየገጠማት ያለው ችግር ከጊዜ ጊዜ የበለጠ እየሰፋና እየተወሳሰበ ነው ተብሏል።
አፍሪካ ከውሃ ጋር በተገናኘ ለሚገጥማት ችግር ክፍተቱ ያለው ጥናትና ምርምር ላይ ሳይሆን የምርምር ስራዎችን ከፖሊሲ፣ በጀት እና ወደ ተግባር ከመቀየር ጋር በተገናኘ በሚፈለገው ልክ መስራት ባለመቻሉ ነው ተብሏል።
