የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት የቀድሞው የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እያገለገሉ የቆዩት ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ቀሪ ሹመቶች፦
• አቶ ጥላሁን ከበደ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
• ዶ/ር አህመዲን መሃመድ – የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
• ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ – የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
• አያልነሽ ኃብተማሪያም (ኢ/ር) – የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ
• ወ/ሪት ጽዮን ደረጀ – የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ
• ህይወት ፀጋዬ (ኢ/ር)- የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ
• ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ – የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ
• ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል – የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ግርማ ሰይፉ – የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ቢኒያም ምክሩ – የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ሙሉቀን ታሪኩ – የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
• ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ – የንግድ ቢሮ ኃላፊ
• ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
• ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
• አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
• ዶ/ር ተፈራ ሞላ – የትራንስፖርት ቢሮ
• አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) – የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
• ሔለን ገመዳ (ኢ/ር) – የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ
• ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ – የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ
• አቶ ተስፋዬ ደጀኔ – የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
• አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
• አቶ መላኩ ታምሩ – የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ
