በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 701 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 531 ወንዶች፣ 144 ሴቶች እና 26 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 32 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ብሏል።
አክሎም ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ነው ያለው፡፡
ከአንድ አመት በፊት ማለትም መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ105 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም ነው ያስታወቀው፡፡
