EthiopiaNews

ጉምሩክ ኮሚሽን ከመስከረም 21 እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከ820 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒቶች፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በጋራ በተደረገ ፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ በተከናወነ ስራ ህገወጥ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 25 ተጠርጣሪዎች እና 14 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በስራው ለተሳተፉ አካላት ምስጋናውን አቅርቦ፣ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡