EthiopiaNews

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ መቀጠሉን አስታወቀ።

ኮሚቴው ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ከጥቅምት 02 እስከ 06፣ 2019 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር አስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎችን እና መድኃኒቶችን ጨምሮ የህክምና ግብአቶችን በትግራይ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ በሰሜን ምዕራብ ዞን ለሚገኘው ሱሁል-ሽሬ ሆስፒታል እንዲሁም በደቡብ ትግራይ ለሚገኙ ማይጨው፣ መሆኒ፣ አላማጣ ሆስፒታሎች እና ጨርጨር ጤና ጣቢያ መከፋፈሉ ተገልጿል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እነዚህ ልገሳዎች የቆሰሉትን ለማከም እና የታመሙትን ለመንከባከብ የሚረዱ ናቸው ብሏል።