ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የ78ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች፡፡
77ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባውን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እያካሄደ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከተለያዩ ሀገራት ተቀብላ በማስተናገድ ላይ መሆኗን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በኮሚሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሊቀመንበርነት መመረጧ ለስደተኞች ጥበቃና እንክብካቤ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ እውቅና መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
መረጃው ከስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የተገኘ ነው
