የአዲስ አበባ ፖሊስ በመዲናዋ በአንድ ቀን ውስጥ በደረሱ ሦስት የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት መድረሱን አስታወቀ።
ፖሊስ አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በተለያዩ ቦታዎች መሆኑን ነው ያስታወቀው።
በዚህም
👉1. ጀሞ ቅዱስ ሚካኤል መብራት ከቀኑ 9፡30 አካባቢ የጉዞ አቅጣጫውን ከአየር ጤና ወደ ጀርመን አደባባይ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-08136 ኢት ሲኖትራክ ተሽከርካሪ መብራት ይዟቸው ቆመው የነበሩ 10 ተሽከርካሪዎችን እና የመብራት ፖል ገጭቷል።
በአደጋው በትራንስፖርት ተሽከርካሪ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ የ44 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አንዲት እናት መሞታቸው በአንድ ሌላ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።
👉2. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ ጀሞ ሦስት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-43228 አ/አ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ይዞ ከጀሞ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ጀሞ ሶስት ሲጓዝ የነበረ አሽከርካሪ ከቀኝ ወደ ግራ ሲሻገር በነበረ ግለሰብ ላይ የሞት አደጋ ማድረሱን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
👉3.በዕለቱ ከምሽቱ 4፡30 አካባቢ ደግሞ ሀጫሉ መንገድ አካባቢ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-52305 አ/አ ሀዩንዳይ ተሽከርካሪን በመያዝ ወደ ጋርመንት እያሽከረከረ የነበረ ግለሰብ ከመንገድ ጠርዝ ጋር በመጋጨት የአሽከርካሪው ህይወት አልፏል።
በክ/ከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ቀን ብቻ በደረሱ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተነገረው።
ፖሊስ አሽከርካሪዎች እና እግረኞች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።
