በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭጌኒ ተረኪን ኢትዮጵያ በአለም ሦስተኛዋ የሩሲያ ማዳበሪያ ገዥ እንደሆነች ተናገሩ።
አምባሳደሩ ይሄን ያሉት ከሩሲያው የዜና ወኪል ታስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግሥት በዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የማዳበሪያ ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።
አምባሳደሩ በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 አመት የሩሲያ ማዳበሪያ አምራቾች የኢትዮጵያን ፍላጎት በማሟላታቸው ምክንያት ኢትዮጵያ በአለም ሦስተኛዋ የሩሲያ ማዳበሪያ ገዥ መሆን ችላለች ብለዋል።
የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የአምራች ዘርፍ ውስጥ ለመሳተፍ ንግግር እያደረጉ መሆኑን አምባሳደሩ ተናግረዋል።
