InternationalNews

ሩሲያ የምትቆጣጠራት የኦሌሽኪ ከተማ የተደረሰው የተኩስ አቁም ዛሬ ተጀምሯል። 

ቀድሞ በዩክሬን ስር በነበረችው ከተማዋ የተኩስ አቁም የተደረገው ከተማዋ በወታደራዊ ፍጥጫ በመከበቧ ለነዋሪዎች ምግብና መድሃኒት ለማድረስ ነው።

የከተማዋ ልዩ ተኩስ አቁሙ የተደረገው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካደራደሩና ባለቤታቸው ሜላንያ ትራምፕ ትግበራውን በይፋ ካወጁ በኋላ ነው።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በቴሌግራም ገፁ ከኦሌሽኪ ማዶ የምትገኘውን ኮርስን ከተማንም ማጥቃት ማቆሙን ገልጿል።

ኦሌሽኪ ከዲንፕሮ ወንዝ ባሻገር ስትገኝ የኮርሰን ቀጠና ዋና የጦር ግምባር ናት።

አሁን በኤሌሽኪ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት ገጥሟቸዋል።