በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች ወደ ሞጆ ሌዘር ኢንዱስትሪ ከተማ እንዲዘዋወሩ እንደሚደረግ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሞጆ ሌዘር ኢንዱስትሪ ከተማ ግንባታን በፍጥነትና በጥራት ወደ ትግበራ ለማስገባት የስራ ጉብኝት ያደረገው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ የመሬት ይዞታዎችን በተመለከተ የካሳ ክፍያዎች ተጠናቀው የመሬት ርክክብ መፈጸሙን አስታወቋል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት 147 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ፕሮጀክቱ የአካባቢ ጥበቃን ባማከለ መልኩ በዜሮ ፈሳሽ ብክለት በቴክኖሎጂ የሚገነባ መሆኑም ተጠቁሟል።
