InternationalNews

የአሜሪካው የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመወጋት የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችለውን “ሊናካፓቪር”  የተባለ መድኃኒት አጸደቀ።

ክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ሊናካፓቪር  በመባል የሚጠራው የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት ለመከላከል የሚያግዘው መድኃኒት መቀመጫውን ጄኔቫ ባደረገው በዶክተር ሬዲስ ላቦራቶሪስ የተዘጋጀ መሆኑ ነው የተነገረው።

ይሄው ሊናካፓቪር የተሰኘው መድሃኒት ለአንድ ሰው በአመት በ40 ዶላር ዋጋ እንደሚቀርብ እና በ120 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት እንደሚሰራጭ ተገልጿል።

አዲሱ መድሃኒት በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 አመት መጨረሻ ጀምሮ መሰራጨት እንደሚጀምር እና በፈረንጆቹ 2027 አመት ደግሞ በስፋት በሀገራቱ ተደራሽ እንደሚሆን ነው የተነገረው፡፡

በየቀኑ መድኃኒት መውሰድ ለሚረሱ ወይም ለሚቸገሩ ሰዎች ይህ መድሃኒት ከፍተኛ መፍትሔ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን፣ ተደርገዋል በተባሉ ጥናቶችም አዳዲስ በኤችአይቪ ኤድስ የመያዝ አጋጣሚዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማስቀረቱ ተረጋግጧል ተብሏል።