InternationalNews

ትላንት በተጀመረው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን የምክር ቤት ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩዎች የሀገሪቱን ሴኔት እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ማሽነፋቸው ታውቋል።

የምርጫው ውጤት መራጮች በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢኮኖሚ አመራር እና ባለፈው የካቲት ወር ከኢራን ጋር በከፈቱት ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የነዳጅ እና የኑሮ ውድነት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ያሳየ ነው ተብሏል።

ዲሞክራቶች ቀደም ሲል ለሪፐብሊካን ፓርቲ ታማኝ በነበሩት እንደ ቴክሳስ፣ ካንሳስ፣ ኦሃዮ እና ደቡብ ካሮላይና ባሉ ግዛቶች ድል ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በቴክሳስ የሦስት ዘመን ገዥ የነበሩት ግሬግ አቦት ጭምር በዲሞክራቷ ጂና ሂኖጆሳ መሸነፋቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ እሳቸው ራሳቸው በምርጫ ካርዱ ላይ እንዳልነበሩ ጠቁመው፣ እሳቸው በዕጩነት ቀርበው ቢሆን ኖሮ ሪፐብሊካን ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ ያሸንፍ እንደነበር አስታውቀዋል።

ታዲያ የወጡት የሕዝብ አስተያየት ውጤቶች እንደሚያሳዩት፤ ሀምሳ በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን ይህንን ምርጫ በፕሬዝዳንቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ የተጠቀሙበት ሲሆን በሌላ በኩል ሰባ በመቶ መራጮች ደግሞ ኮንግረሱ በፕሬዝዳንቱ ላይ ጠንካራ የቁጥጥር ስልጣን እንዲኖረው እንደሚሹ ተመልክቷል።