ሕብረት ባንክ በ2015 ዓ.ም 10 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከግብር በፊትና ከመጠባበቂያ ተቀናሽ በኋላ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር አተረፍኩኝ ብሏል።
ባንኩ ይህን ያለው 26ኛ መደበኛና 13ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን ባካሄደበት መድረክ ሲሆን ፤ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 64 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡
ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወይም የ20 በመቶ የሚጠጋ ጭማሪ ማሳየቱም ባንኩ ለአዲስ ነገር ተናግሯል።