EthiopiaNews

በኢትዮጵያ ከ26 አገራት የተውጣጡ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጉ ስደተኞች በኢትዮጵያ መኖራቸው ተነገረ ።

ይህንንም ከግምት በማስገባት የፍትህ ሚኒስቴር ና አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም በሰዎች መነገድና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እንዲሁም በህጋዊ መንገድ ወደተለያዩ አገራት የሚጓዙ ዜጎችን መብት ለማስጠበቅ ያለመ ስምምነት አድርገዋል።

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ኢትዮጵያ ወደተለያዩ አገራት የሚጓዙ ስደተኞች መነሻና መድረሻ መሆኗ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትኩረትን የሚሻ ነው ብሏል በስምምነቱ ወቅት።

በተጨማሪም ስምምነቱ ከስደት ተመላሾችን የስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ከተለያዩ አገራት ተሰደው በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች በሙያና ቴክኒክ የትምህርት እድል ተሳታፊ ማድረግና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበትን እድል ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል።

ዘገባው የደስዬ ልባይ ነው።