በአዲስ አበባ በ3 ወራት ውስጥ 106 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተነግሯል ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በሩብ ዓመቱ 494 ከባድና 385 ቀላል የአካል ጉዳት ሲመዘገብ ከ8 ሺህ 250 በላይ የንብረት አደጋም መድረሱ ገልጿል።
እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ ተደራሽ በሆነባቸው ቦታዎች 541 ሺህ 420 ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ ለደንብ ጥሰቱ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ናቸው ተብሏል።
ይህም ትርፍ የመጫን፣ የትራፊክ መብራት የመጣስ፣ የደህንነት ቀበቶ አለማሰር፣ ህጋዊ የመንጃ ፈቃድ ሳይዙ ማሽከርከርና ሌሎችም በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው ተብሏል።