InternationalNews

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ሄንሪ ኪሲንጀር በ100 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡

ኪሲንጀር እስከ ቅርብ ጊዜ በአሜሪካ ፖለቲካና ብሄራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆነው ሲቆዩ በተለይ አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት ወደ ጥሩ ምእራፍ እንዲሸጋገር ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
የቀድሞው ከፍተኛ ዲፕሎማት ቻይናን ከ100 ጊዜ በላይ መጎብኘታቸው “የቻይና ህዝብ ወዳጅ” የሚል ቅጽል ስም አሰጥቷቸዋል፡፡
ኪሲንጀር የቪዬትናሙ ጦርነት እንዲቆም እንዲሁም በእስያ መረጋጋት እንዲሰፍን የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደነበርና በፈረንጆቹ 1973 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ እንደነበሩ ሲጂቲኤን በዘገባው አስታውሷል፡፡