EthiopiaNews

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 701 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

‎ሚኒስቴሩ በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 531 ወንዶች፣ 144 ሴቶች እና 26 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 32 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ብሏል።

‎አክሎም ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ነው ያለው፡፡

‎ከአንድ አመት በፊት ማለትም መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ105 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም ነው ያስታወቀው፡፡