EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርጫ ታዛቢ ቡድን በተለያዩ የሀገሪቱ የምርጫ ክልሎች ተሰማርቶ የምርጫ ሂደቱን በመታዘብ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

🔸የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በአርባምንጭ ከተማ ድምፅ መስጠታቸውን እና የምርጫ ሂደቱን ጭምር መታዘባቸውን ተናግረዋል።

🔸በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ምክትል ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ የተመራ የኮሚሽኑ የታዛቢዎች ቡድን ደግሞ በባህርዳር ከተማ የተለያዩ ምርጫ ክልሎች ተዘዋውሮ ጉብኝት ማካሄዱ ነው የተገለጸው።

🔸የባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልሎችን የታዘበው ቡድኑ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንም አሳውቋል

🔸ቡድኑ በቀጣይ ወደ ጎንደር ከተማ አቅንቶ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደሚታዘብም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ጠቁመዋል።

#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv